በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሪዎች ሕግ እንዲተላለፉ የሚያደርግ ነው” ጆ ባይደን


የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዋይት ሀውስ ዋሽንግተን ዲሲ ሃምሌ 1/2024
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዋይት ሀውስ ዋሽንግተን ዲሲ ሃምሌ 1/2024

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ‘የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንቶች በሥልጣን ላይ እያሉ በሠሩት መንግሥታዊ ሥራ ምክንያት እንዳይከሰሱ’ ሲል ትላንት ሐሙስ ያስተላለፈውን ውሳኔ ነቀፉ

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ‘እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2020 የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ለማስቀልበስ ሞክረዋል’ በሚለው ሙግት ላይ ትላንት ውሳኔውን የሰጠ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎም ፕሬዝዳንት ባይደን ትላንት ማታ ከዋይት ሐውስ ባሰሙት ንግግር "ማንም፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንትም ጭምር ከሕግ በላይ አይደለም" ብለዋል። አስከትለውም እሳቸው የፕሬዝዳንታዊ ስልጣን ገደቦችን ማክበራቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸው፤ ወደፊት የሚመጡ ፕሬዝዳንቶች ግን ላያከብሩ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

"ከአሁን ወዲያ ዶናልድ ትረምፕን ጨምሮ የትኛውም ፕሬዝዳንት፣ሕጉን እንደልባቸው መተላለፍ ይችላሉ" ሲሉ ባይደን አስጠንቅቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG