በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የድንበር ቁጥጥር ኅላፊ (ቦርደር ዛር) ሆነው የተሾሙት ቶም ሆማን ትላንት ዕሁድ ባደreጉት ንግግር፤ አስተዳደሩ በአሁን ሰዓት ቅድሚያ የሚሰጠው በሀገሪቱ ደህንነት ላይ ስጋት ይፈጥራሉ የተባሉ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን ማስወጣት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ በአጠቃላይ ማንኛውንም በህገ ወጥ መንገድ የሚደረግ ፍልሰት ሀገሪቱ እንደማትታገስ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
የአሜሪካ ድምጿ ቬሮኒካ ባልደራስ ኤግሊሲያስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም