በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ከኪም ጆንግ ኡን ጋር በቪየትናም የሚያደርጉት ውይይት


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ በዚህ ሳምንት ቪየትናም ውስጥ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር የሚያደርጉት ውይይት ፍሬያማ እንደሚሆን ተነበዩ።

የሁለቱ ውይይት፣ ሰሜን ኮሪያን ከኑክሊየር ጦር መሣሪያ ነፃ በማድረግ ላይ ያተኮረ መሆኑን፣ ዋይት ኃውስ አመልክቷል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ቅዳሜ ዕለት ባሰሙት ቃል፣ «ዐይን ለዐይን እንተያያለን ብዬ አምናለሁ። እናንተ ግን በቀጣዮቹ ቀናት በተደጋጋሚ ታዩታላችሁ» ብለዋል።

«ቬትናም ውስጥ በጣም አስደሳች የሆኑ የሁለት ቀን ተኩል ጊዜ እንደሚኖረን አምናለሁ» ሲሉ ዋይት ኃውስ ለተሰበሰበው የየስቴቶቹ ገዥዎች ቡድን የተናገሩት ትረምፕ፣ «በጣም አደገኛ የሆነ አካባቢን ከኑክሊየር ጦር መሣሪያ ነፃ ለማድረግም መልካም አጋጣሚ ይሆንልናል» ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ «እንግዲህ፣ በሰሜን ኮሪያ በኩል አስፈራ የሆነ የኑክሚየር ሥጋት አይኖርም» ካሉ በኋላ፣ ሁለቱ መሪዎች ባለፈው ሰኔ ወር መገናኘታቸው አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG