በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ለጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኝነት ያጯቸው ብሬት ካቫኖ


ብሬት ካቫኖ
ብሬት ካቫኖ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት ያጯቸውን ብሬት ካቫኖ"ከሥላሳ ሥድስት ዓመታት በፊት አብረዋቸው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በነበሩት ወጣት ላይ ወሲባዊ ጥቃት አድርሰዋል ብዬ ለማሰብ ይከብደኛል" ሲሉ ተናገሩ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት ያጯቸውን ብሬት ካቫኖ

“ከሥላሳ ሥድስት ዓመታት በፊት አብረዋቸው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በነበሩት ወጣት ላይ ወሲባዊ ጥቃት አድርሰዋል ብዬ ለማሰብ ይከብደኛል” ሲሉ ተናገሩ።

ካቫኖ ጥቃቱን አድርሰውብኛል ብለው የወነጀሉዋቸው ሴት ለሕይወታቸው ፈርተው እንደነበር ተናግረዋል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኛውን የወነጀሉዋቸው ካሊፎርኒያ የሚኖሩ የሥነ ልቦና ጥናት ፕሮፌሰር ክሪስብሌይዚ ፎርድ በመጪው ሰኞ የመወሰኛ ምክር ቤት የፍትህ ኮሚቴ ፊት ቀርበው ቃላቸውን ይሰጣሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።

የሃምሳ አንድ ዓመትዋ ክሪስቲን ፎርድ የሚሉትን ለመስማት እፈልጋለሁ ካልቀረቡ ያሳዝናል ሲሉም ትረምፕ አክለዋል።

የፕሮፌሰሯ ጠበቃ በበኩላቸው ደንበኛቸው መወሰኛው ኮሚቴ ፊት ከመቅረባቸው በፊት የፌዴራል ምርመራ ቢሮ ጉዳዩን ኣንዲመረምር ጠይቀዋል። ሚስተር ትረምፕ እና የምክር ቤቱን ኮሚቴ የሚመሩት ሪፐብሊካኖች ግን የኤፍቢአይ ምርመራ አያስፈልግም እያሉ ነው።

እኤአ በ1982 ዋሺንግተን አካባቢ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ውስጥ በአንድ ግብዣ (ፓርቲ) ላይ ጥቃት አደረሱብኝ ተብሎ የቀረበባቸውን ውንጀላ እኔ በአንድም ሴት ላይ ጥቃት ፈፃሜ አላውቅም ሲሉ አጥብቀው ያስተባበሉት ካቫኖ ኮሚቴው ፊት አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ዕጩዋቸውን ግሩም ሰው ሲሉ አወድሰው የሹመታቸው ማፅደቂያ ሂደት በምን ዓይነት እንደሚቀጥል ግን የሚወስነው ምክር ቤቱ ነው ብለዋል።

ይህ በዚህ እኤአ በ1991 በጊዜው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኛ የነበሩትን ክለረንስ ቶማስን በወሲባዊ ጥቃት ወንጅለዋቸው የነበሩት የሕግ ፕሮፌሰር አኒታ ሂል ክሪስቲን ፎርድ በኣካቫኖ ላይ ያቀረቡትን ክስ ኤፍቢአይ ይመርምርልኝ ሲሉ መጠየቃቸውን ደግፈዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG