ዋሺንግተን ዲሲ —
በሪፖብሊካውያን የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በፈለጉት መሰረት የ5ቢልዮን ዶላር ለድንበር ግንብ የሚሰጥ ጊዜያዊ ባጀት ለመመደብ ወስኗል።
በዋሺንግተን ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ እኩለ ሌሊት ላይ ከፊል የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሥራ እንዳይዘጋ የተወነው ባጀት ትላንት ማታ ያለፈው 217 በ185 ድምፅ ነው።
የባጀቱ ውሳኔ ወደ ህግ መወሰኛው ምክር ቤት ይላካል። ከዛም የማለፍ ዕድል የለውም የሚል ግምት አለ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ