በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ክሳቸውን ለመስማት ፍ/ቤት ቀረቡ


የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና ግዙፍ የግንባታ ኩባንያቸው፣ “ለዓመታት ማጭበርበር ፈጽመዋል፤” በሚል የቀረበባቸውን ክስ ለመስማት፣ ዛሬ በኒው ዮርክ በሚገኝ ፍ/ቤት ቀርበዋል።

ትረምፕ፣ ከባንኮች እና ከሌሎችም ተቋማት ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ፣ ሀብታቸውን እጅግ አጋነው በማቅረብ ማጭበርበር ፈጽመዋል፤ የሚል ክስ፣ ባለፈው ሳምንት ተመሥርቶባቸው ነበር።

ትረምፕ ወደ ፍርድ ቤቱ ከመግባታቸው በፊት፣ ክስ ያቀረቡባቸውን ዐቃቤ ሕግ እና ክሱን የሚመለከቱትን ዳኛ አጥላልተዋል። ጥቁር ዐቃቤ ሕጓን፥ “ዘረኛ” ሲሉ፣ ዳኛውን ደግሞ “የማይታመኑ” ብለዋቸዋል።

ከሳሽ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለሊታ ጄምስ፣ በዶናልድ ትረምፕ ላይ የ250 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት እንዲጣልና ወደፊት በኒው ዮርክ ግዛት መኖሪያቸው ከመሥራት እንዲታገዱ እንዲወሰንላቸው ጠይቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG