ዋሺንግተን ዲሲ —
ፕሬዚዳንትት ዶናልድ ትራምፕ፣ ከግራና ቀኝ በመጣ ከፍተኛ ውርጅብኝ ውስጥ ናቸው። ይህም፣ በነጭ ብሔርተኞች ተዘጋጅቶ ባለፈው ቅዳሜ በሻርለትስቪል ቨርጂንያ ለተፈፀመው አመፅ ተጠያቂው ማን እንደሆን የሰጡትን አስተያየት በመለዋወጣቸው ነው።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከትናንት ቤሽቲያ ማክሰኞ ሲናገሩ፣ በሁለቱም ወገን ያሉት ለአመፅ ተጠያቂዎች ናቸው ስላሉ፣ ከዴሞክራቶችም ከሪፖብሊካኖቹም ውግዘት ደርሶባቸው ነበር። ይህም በፕሬዚዳንቱ ላይ የሚሰጠው የሕዝብ አስተያየት መለኪያ ሰንጠረዥ ባሽቆለቆለበት ወቅት መሆኑ ነው።
“ትራምፕ ታወር” በሚባለው በኒው ዮርኩ መኖሪያ ቤታቸው ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ዱላ ቀረሽ መግለጫ፣ ፕሬዚደንቱ በቨርጂንያ የቻርለትስቪልቩ አመፅ፣ በሁለቱም ወገን የነበሩ ተሰላፊዎች ተጠያቂ ናቸው በሚለው በቀደመ አቋማቸው ፀንተዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ