በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትራምፕ የመጀመሪያዋን ወታደራዊ ተቋም የሚመሩ ሴት ከፍተኛ ባለሥልጣን ከኃላፊነት አነሱ


ፎቶ ፋይል፦ አድሚራል ሊንዳ ፋጋን
ፎቶ ፋይል፦ አድሚራል ሊንዳ ፋጋን

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ተቋም በመምራት የመጀመሪያዋ የሆኑትን ሴት - አድሚራል ሊንዳ ፋጋንን ከሥልጣን አነሱ።

ለዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ድንበር እና አካባቢ ጥበቃ ኃላፊነት የተሰጠውን አድሚራል ፋጋን የሚመሩትን ወታደራዊ ተቋም የሚቆጣጠረው የሃገር ውስጥ ደህንነት መሥሪያ ቤት ትላንት ማክሰኞ በፋጋንን ከሥልጣን መነሳት በተመለከተ ዙሪያ አስተያየት እንዲሰጥ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም።

ፋክስ ኒውስ የቴሌቭዥን ጣቢያ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣንን ጠቅሶ ለአድሚራሏ ከሥልጣን መነሳት ምክንያቶቹ የዩናይትድ ስቴትስን ድንበር የደኅንነት ስጋቶችን መፍታት ያለመቻላቸው፣ ብዝሃነት፣ ተደራሽነት እና ሁሉን አቀፍነት ለሚሉት ጉዳዮች የተሰጠ ‘ከልክ ያለፈ’ ያለው ትኩረት፤ እንዲሁም መሥሪያ ቤታቸው የጾታዊ ጥቃትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ያደረገው ምርመራ የፈጠረው “የእምነት መሸርሸር” ይገኙበታል’ ብሏል።

ትራምፕ እና ሌሎች የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪዎች ብዝሃነትን ለማጎልበት የታለሙ የመንግሥት ፕሮግራሞችን በመቃወም ለረጅም ጊዜ ሲተቹ ቆይተዋል። ትላንት ሰኞ ሁለተኛ ዙር ፕሬዝዳንታዊ የሥልጣን ዘመናቸውን አንድ ባሉባት የመጀመሪያ ቀን የሃገሪቱን ድንበር አስመልክቶ የአስቸኳይ ጊዜ ላወጁት ትራምፕ፤ የድንበር ደህንነት ቅድሚያ ከሚሰጧቸው ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG