በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፕሬዚዳንት ትራምፕ እና የፕሬዚዳንት ትራምፕን እገዳ የሻሩት የሲያትሉ ፌዴራል ዳኛ


የሲያትሉ ፌዴራል ዳኛ ጄምስ ሮበርት

በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምክር ቤት አባሎች መካከል አንድ አዲስ ትንቅንቅ ተጀምሯል፡፡

በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምክር ቤት አባሎች መካከል አንድ አዲስ ትንቅንቅ ተጀምሯል፡፡ ይህም ፕሬዚዳንቱ ከሰባት የእስልምና ተከታይ ሀገሮች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገቡ ስደተኞችን ያገደውን ሕግ በሻሩት የሲያትሉ ፌዴራል ዳኛ ላይ የሰጡትን ነቀፌታ ዴሞክራቶችና ሪፖብሊካን በጋራ የመቃዎችማቸው ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ትንቅንቅ እስከ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እንደሚደርስ በመግለፅ ነው፡፡

የፕሬዚዳንት ትራምፕ እገዳ የሻሩት የሲያትሉ ፌዴራል ዳኛ ጄምስ ሮበርት እገዳው የዩናይትድ ስቴትስ ጥቅም በብዙ መልኩ እንደሚጎዳ ሊጠገን የማይችል ስህተት መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

የዳኛ ጄምስ ሮበርት ውሳኔ በአንድ በኩል በመላው የአሜሪካ አውሮፕላን ጣቢያዎች ታላቅ ደስታን ሲፈጥር፣ በሌላ በኩል ትራምፕ ደግሞ

"አደገኛና በብዙ ሰዎች ወደ ሀገራችን ሊገብ ይችላሉ" በማለት ብስጭታቸውንና ንዴታቸውን በትዊትር መግለፅ ጀመሩ፡፡ የዚህ የ"ዳኛ ተብዬ"ውሳኔ የማይረባ ስለሆነ ውድቅ ይደረጋል ሲሉም መኮነን ቀጠሉ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በፕሬዚዳንት ትራምፕ እና የፕሬዚዳንት ትራምፕን እገዳ የሻሩት የሲያትሉ ፌዴራል ዳኛ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:57 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG