በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ከቱርክ በሚገቡ ብረትና አሉሚነም ላይ የተጣለው ታሪፍ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በዛሬው ዕለት ከቱርክ በሚገባ ብረትና አሉሚነም ላይ ከፍተኛ የቀረጥ ጭማሪ በማድረግ ውጥረቱን አባብሰውታል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በዛሬው ዕለት ከቱርክ በሚገባ ብረትና አሉሚነም ላይ ከፍተኛ የቀረጥ ጭማሪ በማድረግ ውጥረቱን አባብሰውታል።

ቱርክ ላይ ታሪፉ በዕጥፍ እንዲጨምርባት ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ ሲሉ ፕሬዚደንቱ በትዊተር አስታውቀዋል።

ሚስተር ትረምፕ ይህን ያደረጉት ቱርክ በሁለቱ ሃገሮች መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ የዲፕሎማሲያዊ ልዑካን ወደ ዋሺንግተን ከሁለት ቀናት በኋላ መሆኑ ነው።

ተንታኞች የሁለቱ ሃገሮች ውጥረት በቱርክ ላይ የገንዘብ ቀውስ አደጋ ደቅኖባታል ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር።

ሚስተር ትረምፕ ቱርክ ወደዩናይትድ ስቴትስ ገበያ ሸጧን ከቀረጥ ነፃ መላኳን ሊያስቆሙ ነው ብለው በወጡ ሪፖርቶች ምክንያት የቱርክ ሊራ በአስር ዓመት ውስጥ ባልታየ መልኩ አሽቆልቁሏል። የዛሬው መግለጫቸው ደግሞ የሊራዋን ዋጋ ይብሱን አወርዶታል።

የቱርክና የዩናይትድ ስቴትስ ውጥረት ባለፈው ሳምንት ይበልጡን የተባባሰው አሜሪካዊው ቄስ አንድሩው ብረንሰን ቱርክ ውስጥ ከመታሰራቸው በተያያዘ ሚስተር ትረምፕ በሁለት የትሩክ ሚኒስትሮች ላይ ማዕቀብ ከጣሉ በኋላ ነው። ቄሱ በሽብርተኝነት ክስ ተስርቶባቸዋል። ዋይት ሃውስ ክሱን መሰረተ ቢስ ብሎ አንካራን“አጋች” ሲል ወንጅሏታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG