በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መ/ቤት በከፊል ከተዘጋ 11ኛ ቀኑን ይዟል

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መሥርያ ቤት በከፊል ከተዘጋ 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ግንብ ለመሥራት የሚያስፈልግ ገንዘብ እንዲመደብ ያቀረቡት ጥያቄ የምክር ቤት አባላት አልተቀበሉትም።

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መሥርያ ቤት በከፊል ከተዘጋ 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ግንብ ለመሥራት የሚያስፈልግ ገንዘብ እንዲመደብ ያቀረቡት ጥያቄ የምክር ቤት አባላት አልተቀበሉትም።

የህግ መመርያ ምክር ቤት አባላት በመጪው ሀሙስ ሥራ ሲጀምሩ የብዙሃነት ቦታ ስለሚኖራቸው ለ11 ቀናት ያህል ተዘግቶ የቆየውን የመንግሥት ሥራ ክፍል ለመክፈት የሚያስችል የባጀት ዕቅድ እናወጣለን ይላሉ።

ዲሞክራቶቹ የምክር ቤት አባላት የሚያሳልፉት የባጀት ዕቅድ የትረምፕ የድንበር ግንብን አያካትትም። ትረምፕ ባስተላለፉት የአዲስ ዓመት መልዕክት፤ በዲሞክራቶች ዕቅደ ሃስብ ላይ ተሳልቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG