በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዚዳንት ትረምፕ ዓመታዊ ንግግር እንደሚዘገይ ተገለፀ


በከፊል የተዘጉ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ፌዴራል መሥሪያ ቤቶችን ለመክፈት እርሣቸውና ምክር ቤቱ መፍትሄ እስኪያገኙ ድረስ - ከምክር ቤቱ ለሕዝብ በቀጥታ የሚያደርጉትን ንግግር እንደሚያዘገዩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስታወቁ።

በከፊል የተዘጉ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ፌዴራል መሥሪያ ቤቶችን ለመክፈት እርሣቸውና ምክር ቤቱ መፍትሄ እስኪያገኙ ድረስ - ከምክር ቤቱ ለሕዝብ በቀጥታ የሚያደርጉትን ንግግር እንደሚያዘገዩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስታወቁ።

ቀደም ሲል የዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት ሲናገሩ - መሥሪያ ቤቶቹ ተዘግተው እስከቆዩ ድረስ - የፖለቲካ ስብሰባዎችን ጨምሮ - የፕሬዚዳንቱ ዓመታዊ ንግግር ከሌላ ቦታ ሊደረግ እንደሚችል ዕቅዶች አሉ ብለው ነበር።

ፕሬዚዳንቶች የሃገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታዎች አስመልክቶ በየዓመቱ አንድ ጊዜ ለምክር ቤቱ ሪፖርት እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ።

በዚህ ዓመት ግን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መዘጋታቸውን ተከትሎ በፕሬዚዳንቱና በዲሞክራቲክ ፓርቲው መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሯል። አፈ ጉባዔ ናንሢ ፔሎሲ - የመሥሪያ ቤቶቹ መዘጋት የደኅንነት ጥበቃ ሠራተኞችንም ስለሚመለከት ፕሬዚዳንቱ የሚያደርጉትን ዓመታዊ ንግግር ለሌላ ጊዜ እንዲያስተላልፉ ጠይቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ ግን ሥጋት ይኖራል የሚለውን ሃሳብ ውድቅ በማድረግ ንግግሩን የፊታችን ማክሰኞ በተያዘለት ሰሌዳ መሠረት አደርጋለሁ ሲሉ ለምክር ቤቱ በላኩት ደብዳቤ አስታወቁ።

አፈጉባዔ ናንሢ ፔሎሲ በበኩላቸው በሰጡት ምላሽ ሁሉም የተዘጉ መሥሪያ ቤቶች እስኪከፈቱ ድረስ ፕሬዚዳንቱ ከምክር ቤት ንግግር አያደርጉም በሚለው አቋማቸው እንደሚጸኑ ግልጽ አድርገዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG