በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ከ18 ወራት በኋላ ወደ ዋሺንግተን ተመለሱ


የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከዋይት ሃውስ ከወጡ ወዲህ ትናንት ማክሰኞ ለመጀመሪያው ጊዜ ንግግር ለማሰማት ወደ ዋሽንግተን ተመልሰዋል።

ትረምፕ ከዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት አንድ ኪሎ ሜትር ተኩል አካባቢ ርቀት ላይ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ የርሳቸውን አስተዳደር አጀንዳ የሚያራምድ ተቋም በጠራው ስብሰባ ላይ ተገኝተው 600 ለሚሆኑ ደጋፊዎቻቸው ባደረጉት 90 ደቂቃ የቆየ ንግግራቸው በአብዛኛው በህዝብ ደህንነት ላይ አተኩረዋል።

በጥቅምት 2013 ዓ.ም. መጨረሻ በተደረገው ምርጫ “ባይደንን አሸንፌያለሁ” የሚለውን የሀሰት ትርክታቸውን በድጋሚ ማሰማታቸው ተዘግቧል።

“ለፕሬዚዳንትነት ተወዳደርኩ አሸነፍኩ፤ እንደገናም ለሁለተኛ ጊዜ አሸነፍኩ፤ ሁለተኛው ላይ እንዲያውም የተሻለ ድምፅ ነበር ያገኘጉት፤ በጣም የተሻለ ነበር” ብለዋል።

ትረምፕ ታኅሳስ 28/2013 ዓ.ም. የሃገሪቱን የተወካዮች ምክር ቤት ህንፃን (ካፒቶልን) በሁከት የወረሩ ደጋፊዎቻቸውን አድራጎት ተከላክለዋል።

“በወንጀል የተከሰሱስት አንዳንዶቹ ተከላካዮች የተሰተናገዱበት መንገድ በጣም መጥፎ ነበር” ብለዋል የቀድሞው ፕሬዚዳንት ትረምፕ የምርጫውን ድምፅ ሊያፀድቅ የተቀመጠውን ጉባዔ ለማስተጓጎል የተቃጣውን የአመፅ ጥቃት የሚመርምረውን የምክር ቤቱን መርማሪ ኮሚቴም በብዙ ተችተዋል።

እኤአ በ2024 በሚካሄደው መጭው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩ ስለመሆኑ በቀጥታ ባይናገሩም “እርሳቸው የማይወዳደሩ ከሆነ አገሪቱ ትልቅ ጉዳት ያገኛታል” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG