በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕን ጉዳይ የሚያየው ችሎት ለመጪው መጋቢት ተቀጠረ


የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ እ.አ.አ 2016 ከተደረገው ምርጫ በፊት፣ ለወሲብ ፊልሞች ተዋናዪቷ የፈጸሙትን ክፍያ ለመደበቅ፣ “የንግድ ሰነዶችን አጭበርብረዋል፤” በሚል የቀረበባቸውን ክሥ በተመለከተ፣ የሚካሔደው የችሎት ክርክር፣ ለመጪው ዓመት መጋቢት ወር ተቀጥሯል።

ትረምፕ፣ ትላንት በኒው ዮርክ በሚገኘው ፍርድ የቀረቡት፣ በርቀት በቪዲዮ አማካይነት ሲኾን፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት፣ ማስረጃዎችን ቀድመው ከማውጣት እንዲቆጠቡ ዳኛው አስጠንቅቀዋል። ትረምፕ፣ በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ሰዎችን ስለሚያሸማቅቁና ስለሚያጠቁ፣ የዳኛው ትዕዛዝ አስፈላጊ እንደኾነ፣ ዐቃቤ ሕጉ ተናግረዋል።

ትረምፕ የተከሠሡት፣ የወሲብ ፊልም ተዋናዪቱን ዝም ለማሰኘት የከፈሉት ገንዘብ እንዳይታወቅ፣ የንግድ ሰነዶችን አጭበርብረዋል፤ በሚል ነው።

ትረምፕ ለቀረቡባቸው 34 ተያያዥ የወንጀል ክሦች፣ “ጥፋተኛ አይደለኹም፤” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG