ዋሺንግተን ዲሲ —
አፍሪካዊ አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ ቁጥጥር ሆኖ ህይወቱ ማለፉ ለቀሰቀሰው ሃገርቀፍ ተቃውሞ የሚሰጠውን ምላሽ እያጤኑ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ በቴክሳስዋ ዳላስ ከተማ ከሃይማኖት መሪዎች ከሕግ አስከባሪ ባለሥልጣናትና ከአንስተኛ ንግድ ድርጅቶች ባለቤቶች ጋር ይወያያሉ።
የክብ ጠረጴዛ ውይይቱ "በአሜሪካ ማኅበረሰቦች ውስጥ ስላልሉት ታሪካዊ የኢኮኖሚ የጤና እና የፍትኅ ልዩነቶች መፍትሄ ማምጣት ላይ ያተኮረ እንደሚሆን ዋይት ሃውስ ገልጿል።
የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ኬይሊሜኪናንኒ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል አስተዳደሩ በምክር ቤት የቀረቡ ሃሳቦችንና አስፈጻሚ ትዕዛዞችን እየተመለከተ መሆኑን ጠቁመው፣ በቁጣዮቹ ቀናት ውስጥ ያስታውቃል ብለዋል።