በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሥልጣናቸው ግፊት የበዛባቸው ትረምፕ ስለ አመጹ ተናገሩ


በሥልጣናቸው ግፊት የበዛባቸው ትረምፕ ስለ አመጹ ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:23 0:00

በሥልጣናቸው ግፊት የበዛባቸው ትረምፕ ስለ አመጹ ተናገሩ

ፕሬዘዳንት ትረምፕ ትናንት በቪዲዮ ተቀርጾ በወጣው መልዕክታቸው፣ በዚህ ሳምንት ደጋፊዎቻቸው የተወካዮች ምክርቤት ህንጻን በመውረር፣ ያሳዩት አመጽ፣ ሁከትና ህገወጥነት ያስቆጣቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአመጹን ድርጊት ተክትሎ፣ "ትረምፕ ከሥልጣን መወገድ አለባቸው" ከሚሉ የዴሞክራቲክና ሪፐርብሊካን ፓርቲ አባላትም ከፍተኛ ግፊት እየደረሰባቸው ነው፡፡

በዚህ ሳምንት፣ በፕሬዚዳንት ትረምፕ ደጋፊዎች ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ምክር ቤት ህንጻ ላይ የተካሄደው ወረራ፣ ከብዙ ሰዎች ጭንቅላት ውስጥ ገና አልወጣም፡፡ ፕሬዚዳንት ትረምፕ አመጹን አስመልክቶ፣ ትናንት ሀሙስ፣ ምሽቱ ላይ፣ በቪዲዮ ምስል ያሰራጩት መግለጫ የወጣው አገሪቱ በዚህ ስሜት ውስጥ እንዳለች ነው፡፡

"እንደ ሁሉም አሜሪካውያን በአመጹ ህወገጥነቱና ሁከቱ በጣም አስቆጥቶኛል፡፡"

ትረምፕ፣ ምክርቤቱ የምርጫውን ውጤት በማረጋገጥ ማጽደቁን ቢቀበሉም፣ ባለው ልማድ መሠረት፣ ለተመራጩ ፕሬዚዳንት የሚላከውን የእንኳን አደረሰህ መልዕክት በንግግራቸው ውስጥ አልጨመሩም፡፡ እንዲህ አሉ

"አሁን የኔ ትኩረት ሰለማዊው የሥልጣን ሽግግር፣ ያለምንም እንከን፣ በተገቢው ስርዓት መካሄዱን ማረጋገጥ ነው፡፡"

ጆ ባይደን፣ ከትረምፕ ንግግር ቀደም ብለው ሀሙስ ጧት ባሰሙት ንግግር፣ ትረምፕን በድጋሚ ገስጸዋቸዋል፡፡

"በተቋሞቻችና ዴሞክራሲያችን ላይ በሁሉም መስክ ጥቃት መፈጸም የጀመሩት፣ ገና ከመነሻው ጀምረው ነው፡፡ ትናንት ያደረጉትም የዚያ የማያማቋረጠው ጥቃት ድምር ውጤት ነው፡፡"

ባይደን ፕሬዚዳንት ትረምፕ አመጹ እንዲቀሰቀስ በማድረጋቸው፣ ከሥልጣን መወገድ ይገባቸዋል የሚለውን ውትወታ አስመልክቶ በንግግራቸው ውስጥ ምንም ያሉት ነገር የለም፡፡ መጭው የእንደራሴዎች ምክር ቤት መሪ ይሆናሉ የተባሉት ቻክ ሹመርና የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፖሎሲ ግን፣ ፕሬዚዳንቱን በብቃት ጉድለት ከሥራቸው እንዲወገዱ የሚያስችለውንና የተሻሻለውን የህግመንስቱን አንቀጽ 25 በመጥቀስ፣ እየወተወቱ ነው፡፡ እንዲህ ይላሉ ፐሎሲ

"በትናንትናው እለት የተካሄደውን አመጽ በማነሳሳታቸው ከሥልጣናቸው የግድ መወገድ ይገባቸዋል፡፡ ገና 13 ቀን የሚቀራቸው ቢሆንም፣ የትኛውም ቀን፣ በአሜሪካ ዘግናኝ የሆነ ክስተት የሚታይበት ቀን ሊሆን ይችላል፡፡"

የሪፐብሊካን ፓርቲው የተወካዮች ምክር ቤት አባል አዳም ኪንዚንገርም በኩላቸው እንዲህ ብለዋል

"ሁሉም ነገሮች የሚያሳዩት፣ ፕሬዘዳንቱ ከኃላፊነታቸውና ሌላው ቀርቶ የገቡትን ቃለ መሃላ የዘነጉ ብቻ ሳይሆኑ፣ ካለው እውነታ ራሱ እጅግ የራቁ ናቸው፡፡"

የህገመንግስቱ የማሻሻያ አንቀጽ 25፣ ተግባርና ኃላፊነቱን በሚገባ መወጣት ያልቻለን ፕሬዚዳንት፣ በምክትል ፕሬዚዳንቱና በአብዛኞቹ የካቢኔ አባላት ድምጽ ማስወገድ የሚቻልበትን አግባብ ይፈቅዳል፡፡ ከምክትል ፕሬዚዳንቱም ሆነ ከካቢኔ አባላቱ ግን ይህንን እርምጃ በመደገፍ ድምጹን ያሰማ የለም፡፡ ይህን አስመልክቶ ከአሜሪካ ኤንተርፕራይዝ ተቋም ጆን ፎርቲየ እንዲህ ይላሉ

"ከቀሩት ቀናት አንጻር፣ በህግም ሆነ እርምጃውን ተግባራዊ ከማድረጉ አንጻር አንዳንድ መሰናክሎች ሊገጥሙ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ መደረጉን ሊደረግ ይችል ይሆናል፣ ይሁን እንጂ ግን በጣም በጣም አስቸጋሪ ይሆናል፡፡"

በሌላም በኩል፣ የፌደራል አቃቢ ህግ፣ በተካሄደው አመጽ ዙሪያ ምርመራ እንደሚያደርግና፣ ወንጀለኞችም ላይ ከስ እንደሚመስረት አስታውቋል፡፡ ያ ምናልባትም፣ የምክር ቤት አባላት፣ የምርጫውን ውጤት በማጽደቅ የባይደንን አሸናፊነት እንዳያረጋግጡ፣ ደጋፊዎቻቸውን ወደ ምክር ቤቱ ህንጻ እንዲያመሩ በመገፋፋት፣ አመጹን አነሳስተዋል የሚባሉትን ፕሬዚዳንት ትረምፕንም የሚጨምር ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል፡፡

ትረምፕ “በምርጫው ልሸነፍ የምችለው ምርጫው ከተጭብረበረ ብቻ ነው” የሚለውን ለወራት ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡ በጋርዮሽ ከሚሰራው የፖለሲ ተቋም ጄሰን ጋርመት እንዲህ ይላሉ፤

"እሚታዩት ምስሎች በጣም አስደንጋጭና አሳዛኝ ናቸው፡፡ እና እኔ እንደሚመስለኝ፣ እንዳለመታደል ሆኖ፣ ፕሬዚዳንቱ ለዴሞክራሲ ካላቸው ንቀት አንጻር፣ ውጤቱ ይህ ሊሆን እንደሚችል ሲጠበቅ የቆየ ይመስለኛል፡፡

አፈጉባኤዋ ናንሲ ፐሎሲ፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ የህግ መንግስቱን ማሻሻያ አንቀጽ 25 በመጥቀስ ምንም እንቅስቃሴ የማያደርጉ ከሆነ፣ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንቱን ከሥልጣናቸው ለማንሳት፣ የሚያስችለውን የፖለቲካ ውሳኔ ይሰጣል ብለዋል፡፡ ትረምፕ እኤአ በ2019 መገባደጃው ላይ፣ ከሥልጣናቸው እንዲነሱ በተወካዮች ምክር ቤት የፖለቲካ ውሳኔ የተላለፈባቸው ቢሆንም፣ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት፣ እኤአ የካቲት 2020 ሳይደግፈው በመቅረቱ ውሳኔው ውድቅ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ዘገባው በቪኦኤ የዋይት ሀውስ ዘጋቢ የፓትሲ ውዳክስዋራ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG