ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፐሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ስቶርሚ ዳኒኤልስ “ፖርን” የወሲብ ሲኒማ ለታወቅችው ሴት አፍ ማዘጊያ $130,000 ዶላር መከፈሉን አረጋግጠዋል።
እአአ በ2006 ከፕሬዚዳንቱ ጋር በኔቫዳ ሄቴል ተኝቻለሁ የምትለው ስቶርሚ ዳንኤልስ ሚስጥር እንዳታወጣ ተብሎ ነው ባለፈው አመት ከተደረገው ምርጫ በፊት ገንዘብ የተከፈላት። ይሁንና ገንዝቡ የተከፈለው ለምርጫ ዘማቻ ከተዋጣላቸው ገንዘብ እንዳልሆነ ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።
ገንዘቡ የተከፈለው ጠበቃቸው በነበረው ሰው በኩል ሲሆን ለጠበቃው በየወሩ እንደከፈሉት ገልፀዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ