በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ የሲአይኤ ዳይሬክተር ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውን አረጋገጡ

Trump Confirms CIA Chief Met with Kim Jong Un
Trump Confirms CIA Chief Met with Kim Jong Un

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የአሜሪካ የመረጃ ድርጅት ሲአይኤ ዳይሬክተር ማይክ ፖምፒዮ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር በሚስጥር ተገናኝተው ተነጋግረዋል የሚለውን ዜና “ትክክል ነው” ሲሉ ዛሬ አረጋገጡ።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የአሜሪካ የመረጃ ድርጅት ሲአይኤ ዳይሬክተር ማይክ ፖምፒዮ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር በሚስጥር ተገናኝተው ተነጋግረዋል የሚለውን ዜና “ትክክል ነው” ሲሉ ዛሬ አረጋገጡ።

“ውይይቱ ያለ እንቅፋት ነው የተካሄደው” ሲሉ በትዊተር ባስተላለፉት መልዕክት የገለፁት ፕሬዚዳንት ትረምፕ “በሁለቱ ወገኖች መካከል መልካም ግንኙነት ተመስርቷል” ብለዋል።

በፕሬዚዳንት ትረምፕ እና በሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ጆንግ ኡን ጋር ወደፊት ሊካሄድ የታቀደውን ጉባዔ አስመልክቶም ዝርዝሩ ትኩረት ተሰጥቶት በመሠራት ላይ መሆኑን፤ ትረምፕ ገልፀዋል።

“ከኒውክሌ የጦር መሳሪያ የፀዳ አካባቢ መፈጠር ለዓለም ታላቅ ክንዋኔ ነው፤ ለሰሜን ኮሪያም እንዲሁ፤” ነው ያሉት።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ በትላንትናው ዕለት ዝርዝር ባልሰጡበት ሌላ አስተያየታቸው ሁለቱ ሀገሮች “በከፍተኛ ባለ ሥልጣናት ደረጃ ተነጋግረዋል” ብለው ነበር።

ትላንት በደቡባዊ ዩናይትድ ስቴትሷ የፍሎሪዳ ክፍለ ግዛት በሚገኝ የባሕር ዳርቻ ከፕሬዚዳንት ትረምፕ ጋር ተገናኝተው የተነጋገሩት የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለመነጋገር ዕቅድ መያዛቸውን እንዲህ ያለው እርምጃ “ቆራጥነትን” ይጠይቃል ሲሉ አወድሰዋቸዋል።

ነገሮች እንደ አያያዛቸው በመልካም ከቀጠሉ፤ በሁለቱ ሀገሮች መካከል የታቀደው ጉባዔ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በሰኔ መጀመሪያ ወይም ከዚያ ጥቂት ቀደም ብሎ ሊካሄድ ይችላል ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG