የዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ የምርጫ ዘመቻቸው ከሩሲያ ጋር “አለው” የተባለውን ግንኙነት ምርመራ እንዲያቋርጥ ሰፊና ተደጋጋሚ ጥረቶች በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኩል ተካሂደውበታል ሲሉ የቀድሞው የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ጄምስ ኮሜ ተናግረዋል።
ሚስተር ኮሜ ትላንት ለሴኔቱ የደህንነት ኮሚቴ የምስክርነት ቃል በሰጡበት ወቅት ያቀረቧቸው እነዚህ ክሶች ማረጋገጫ አልተገኘላቸውም።
እውነት ሆነው ከተገኙ ግን ወትሮ ኤፍቢአይ ሌላ ፕሬዚዳንት አንቆ ይዞ ምርመራውን ወዳጠናቀቀበት ታሪክ የሚወስድ ይሆናል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ