ለዚህ ጉባዔ ታዲያ የዶናልድ ትራምፕ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትነት መመረጥ በጎ ዜና አልነበረም፡፡
“የብርድ ስሜት ለቆበታል” ያሉ ብዙ ናቸው፡፡
የሞሮኮ ጉባዔ አጀንዳ በአለፈው ዓመት ፓሪስ ላይ ለተፈረመው
"እጅግ ታሪካዊ" የተባለ የአየር ንብረት ዓለም አቀፍ ስምምነት አፈፃፀም የፖሊሲ ዝርዝሮችን ማውጣት ነው፡፡
ትራምፕ ግን ያንን ዩናይትድ ስቴትስ የፈረመችውን ስምምነት እንደሚቀዱ ዝተዋል፡፡ የተዘጉ የከሰል ድንጋይ ቁፋሮና ማምራቻ ተቋማትን እንደገና እንደሚከፍቱ የተፈጥሮ ዘይት ልማትና ብዝበዛ ፕሮጀክቶችን እንደሚያጠናክሩና እንደሚገፉባቸው ተናግረዋል፡፡
መጭው የትራምፕ አስተዳደር በእውኑ ለፓሪስ ስምምነት አስደንጋጭ አደጋና ብርቱ ሥጋት ነው፡፡
የዓለማችን የአየር ንብረት ለውጥ ለመቆጣጠርና ለመለማመድ ለሚደረገው ጥረት የጀርባ በረዶ ነው፡፡
አሜሪካ ብሎክ ደሴት ላይ የመሠረተችው በንፋስ ኢነርጂ ማመንጫ ፕሮጀክት በዚህ በያዝነው ወር ውስጥ ሙሉ ሥራ ይጀምርና ለ17ሺሕ ቤቶች የኤሌክትሪክ ኃይል ያቀርባል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ከዋናው መሬቷ ውጭ ባህር ላይ ያቋቋመችው የመጀመሪያው የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ነው፡፡
ይህንን የኃይል ማመንጫ ለመገንባት ስምንት ዓመታትን ጠይቋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ በእነዚህ ባለፉት ስምንት ዓመታት የአየር ንብረት ለውጥን ለመጋፈጥ የመሪነቱን ድርሻ ለመጫወት በብርቱ ስትጥር ቆይታለች፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡