በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና የንግድ ድርድር


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና የንግድ ድርድር እየተቃረበ ባለበት ባሁኑ ሰዓት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ስምምነቱ ከመጪው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ እንዳይሆን ቻይናን ማስጠንቀቅ ይዘዋል።

የንግድ ስምምነቱ ዘግይቶ ቢከናወን ወደ በምርጫው ዋዜማ ቢሆን በሚያረካቸው ደረጃ አይሆንም ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ በትዊተር ባወጡት ቃል “ቻይና ስምምነቱን ካዘገየችው በምርጫው ያሸነፍኩ እንደሆን ወይም ሳሸንፍ የሚያገኙት ስምምነት አሁን ከምንደራደርበት ውል ይበልጡን የጠነከረ ይሆናል ወይም ጨርሶ ስምምነት ላይ ላይደረስ ይችላል” ማለታቸው ተጠቅሷል።

ፕሬዚደንት ትረምፕ ይህን ያሳሰቡት የዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና ባለሥልጣናት ሻንጋይ ውስጥ ተሰብስበው ድርድሩን ለማንቀሳቀስ እየሞከሩ ባሉበት ባሁኑ ወቅት ነው። ሁለቱም ወገኖች ከስብሰባው ትልቅ ውጤት እንዳይጠበቅ ለመከላከል እየሞከሩ ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG