በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ወደ ላቲን አሜሪካ ሊያደርጉ ያቀዱትን ጉዞ ሰረዙ

ዋይት ኃውስ በሰጠው መግለጫ፤ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በዚህ ሳምንት ማብቂያ ገደማ ወደ ላቲን አሜሪካ ሊያደርጉ ያቀዱትን ጉዞ መሰረዛቸውን አመልክቶ፤ ሦርያን በተመለከተ የዩናይትድ ስቴትስን ምላሽ ለመከታተል መሆኑንም አስታውቋል።

ዋይት ኃውስ በሰጠው መግለጫ፤ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በዚህ ሳምንት ማብቂያ ገደማ ወደ ላቲን አሜሪካ ሊያደርጉ ያቀዱትን ጉዞ መሰረዛቸውን አመልክቶ፤ ሦርያን በተመለከተ የዩናይትድ ስቴትስን ምላሽ ለመከታተል መሆኑንም አስታውቋል።

ለፕሬዚዳንት ትረምፕ ቀደም ሲል የተያዘው ዕቅድ በሊማ፣ ፔሩ በሚካሄደው 8ኛ የአሜሪካ ጉባዔ ላይ መካፈልና ወደ ቦጎታ፣ ኮሎምቢያ መጓዝ እንደነበርም ተገልጧል።

በፕሬዚፋንት ትረምፕ ጥያቄ መሠረትም፣ ምክትል ፕሬዚደንቱ የላቲን አሜሪካውን ጉዞ እንደሚያደርጉ ተገልጧል።

ፒሩ ውስጥ የሚካሄደው ጉባዔ የሚጀምረው የፊታችን አርብ መሆኑም ታውቋል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ፤ ሦርያ በሽምቅ ተዋጊዎች ይዞታ ሥር በሆነው ምሥራቃዊ ጉታ ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ ላደረሰችውና 40 ሰዎች ለሞቱበት የኬሚካል ጦር መሣሪያ ጥቃት፣ ጠንካራ እርምጃ ለመውሰድ ማስጠንቀቃቸው ይታወቃል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG