የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፤ በመጭው ሰኔ አምስት ቀን ሲንጋፖር ውስጥ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ዦንግ ኡን ጋር ሊያደርጉ የታቀደውን ውይይት ሰረዙት። ይህንንም ለሰሜን ኮሪያው መሪ በላኩት ደብዳቤ መግለፃቸው ታውቋል።
ትረምፕ ለፕሬዚዳንት ኪም ከዋይት ሀውስ በተላከ ደብዳቤያቸው፣ “ከእርስዎ ጋር ለመገናኘር በጣሙን ፈልጌ ነበር” ሲሉ ይጀምሩና፣ በመቀጠልም፣ “ሆኖም በቅርቡ ባሰራጩት ግልጥ የጥላቻና አናዳጅ መግለጫዎ ምክያት፣ ይህን ለረዥም ጊዜ ያቀድነውን ውይይት ለማካሄድ ወቅቱ አሁን አይደለም፣ አዝናለሁ» ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ትረምፕን ያስቆጣቸው የመጨረሻው ከሰሜን ኮሪያ ምክትል የውጩ ጉዳይ ሚኒስትሯ Choe Son Hui ዛሬ ጧት፣ የዩናይትድ ስቴትሱን ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስን “የፖለቲካ ደደብ” ብለው በመሳደባቸው መሆኑም ተገልጿል።
የዋይት ሀውስ ባለሥልጣናት በሰጡት መግለጫ፣ ሰሜን ኮሪውያን ፈቃደኛነቱ ካላቸውና አሁን የተያያዙትን ስድብና ኃይለ ቃል ካቆሙ፣ “ወደ ድርድሩ የመግቢያ በር ሁሌም ክፍት ነው” ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ