በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ሩሲያ በG-7 የመሪዎች ጉባዔ ለመካፈል መጋበዝ አለባት አሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

ሩስያ ጂ ሰባት ባለጸጎቹ ሃገሮች የመሪዎች ጉባዔ ላይ እንድትካፈል መጋበዝ አለባት ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ።

ሩስያ G-7 ባለጸጎቹ ሃገሮች የመሪዎች ጉባዔ ላይ እንድትካፈል መጋበዝ አለባት ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱ የመሪዎቹ ጉባዔ ወደሚካሄድባት ወደካናዳ ለመጓዝ ከዋይት ኃውስ ሲነሱ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል “ሩስያን ከማንም በላይ የሚያባንናት ሰው ቢኖር እኔ ነኝ ያ እንዳለ ሆኖ ጉባዔው ላይ መገኘት አለባት” ብለዋል።

አንድ ሌላ የG-7 አባል ሃገር መሪ የኢጣሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ የሚስተር ትረምፕ ሃሳብ ደግፈው በትዊተር ጽፈዋል።

የጉባዔው አስተናጋጅ ሃገር የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ሃገራቸው የሩስያን ማኅበሩን ተመልሳ እንድትቀላቀል መፈቀድ መቃወሟን ትቀጥላለች ሲሉ አስታውቀዋል።

የክሬምሊኑ ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ግን እሰጥ አገባውን ከምንም ባለመቁጠር “ሩስያ ትኩረቷን ሌሎች መድረኮች እያዋለች ነው” ማለታቸውን ስፐትኒክ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

እአአ በ1997 ሩስያ ማኅበሩን መቀላቀለዋን ተከትሎ በዓመቱ ጂ ስምንት ተብሎ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ሩስያ የዩክሬይን ግዛት የሆነችውን ክሬሚያን እአአ በ2014 ወርራ ከያዘች በኋላ ከቡድኑ ታግዳለች። ባለፈው ዓመት ነው ሞስኮ ከነጭራሹ ከቡድናችሁ ወጥቻለሁ ስትል ያስታወቀችው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG