የአሜሪካ መንግሥት ዓመታዊ በጀትን ለማጽደቅ ምክር ቤቱ ድርድር በማድረግ ላይ ባለበት ወቅት ድርድሩ የዕዳ ጣራን ከፍ የማያደርግ ከኾና መንግሥት የሚዘጋ ከኾነ
“አሁኑኑ ይዘጋ” ሲሉ ትረምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የመንግሥት በጀት ዛሬ እኩለ ሌሊት ላይ የሚያልቅ ሲኾን፣ መክር ቤቱ ቀጣይ በጀት የማያጸድቅ ከኾነ በርካታ የመንግሥት ተቋማት ከነገ ጀምሮ ሥራ ያቆማሉ።
በትረምፕ አማካይነት ትላንት ሐሙስ የቀረበውና የሀገሪቱ የዕዳ ጣሪያ ከፍ እንዲል ጥያቄ ያዘለው የበጀት ሐሳብ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዓባላትም ጭምር በመቃወማቸው ውድቅ ሆኗል። ትረምፕ ዛሬ ጠዋት በሰጡት ምላሽ የበጀት ጣሪያው ከፍ የማይል ከኾነ መንግሥት “አሁኑኑ ይዘጋ” ብለዋል።
ገና ቃለ መሃላ ያልፈጸሙት ትረምፕ በጀትን በተመለከተ ያላቸውን ጥያቄ ያቀረቡት፣ የአሜሪካው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ማይክ ጃንሰን ዛሬ ማለዳ በካፒቶል ተገኝተው ትላንት ምሽት የትረምፕን ሐሳብ ውድቅ ካደረጉ ወግ አጥባቂ የሪፐብሊካን ዓባላት ጋራ ምክክር በሚያደርጉበት ወቅት ነው።
ዛሬ እስከ እኩለ ሌሊት በበጀቱ ላይ ስምምነት የማይደረስ ከሆነ፣ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በጀት ስለማይኖራቸው ይዘጋሉ። “አስፍላጊ” ተብለው ከተቀጠሩ ውጪ ያሉ ሠራተኞች በጀት እስኪለቀቅ ድረስ ሥራ እንዲያቆሙም ይደረጋል።
ማይክ ጃንሰንና ሌሎች የምክር ቤት ዓባላት፣ የመንግሥትን ሥራ መዘጋት አሜሪካውያንን ይጎዳል የሚል ፍራቻ ሲያድርባቸው፣ ትረሞፕ ግን መንግሥትን መዝጋት እንደማያስጨንቃቸው የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።
ወደ ሥልጣን ተመልሶ የሚመጣው የትረምፕ አስተዳደር የፌዴራል መንግሥቱን በጀት ለመቀነስና በሺሕ የሚቆጠሩ የመንግሥት ሠራተኞችን ለማባረር እንድሚሻ ይፋ ድርጓል።
ትረምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው፣ የዛሬ አራት ዓመት ገደማ፣ በገና እና ዐዲስ ዓመት ወቅት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በታሪክ ረጅም ለተባለ ጊዜ እንዲዘጉ አድርገዋል።
መድረክ / ፎረም