በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ በኢሚግረሽ ፖሊስ የሚካሄደው ንግግር መቆም ተጠያቂዎች ዲሞክራቶች ናቸው አሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የኢሚግረሽን ፖሊስን አስመልክቶ የሚካሄደው ንግግር ባለበት መቆም ተጠያቂዎች ዲሞክራቶች ናቸው ሲሉ ዛሬ ነቅፈዋል።

የትረምፕ አስተዳደርና የምክር ቤት አባላት ሌላ ከፊል የመንግሥት መሥርያ ቤቶች መዘጋትን ለማስወገድ እየጣሩ ናቸው።

“ዲሞክራቶቹ ወንጀለኛ ባዕዳንን እንድናስር ወይም ወደ መጡበት እንድንመልስ አይፈልጉም። ይህ አዲስ ጥያቄም እብደት ነው” ይላሉ ትረምፕ በትዊተር ባስተላለፉት መልዕክት።

ጭቅጭቁ የተነሳው ትረምፕ ከሜክሲኮ ጋር በሚዋሰነው ድንበር ግንብ ለመገንባት $5.7 ቢልዮን ዶላር እንዲመደብ በመጠየቃቸው ሲሆን የሚካሄደው ድርድር ሌላ ነጥብ አስነስቷል። ዲሞክራቶች በዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግረሽን ባለሥልጣኖች የሚታሰሩት አገር ውስጥ ያሉት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ፍልሰተኞች መጠን ውሱን እንዲሆን ይፈልጋሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG