በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትራምፕና ባይደን ከመራጮች ጋር ለጥያቄና መልስ ተገናኙ


ትራምፕና ባይደን ከመራጮች የሚነሱ ጥቃቄዎችን ለመመለስ በትናንትናው እለት፣ የአዳራሽ ውስጥ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ትራምፕና ባይደን ከመራጮች የሚነሱ ጥቃቄዎችን ለመመለስ በትናንትናው እለት፣ የአዳራሽ ውስጥ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና ተፎካካሪያቸው የቀድሞ ም/ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከመራጮች የሚነሱ ጥቃቄዎችን በቀጥታ በትናንትናው እለት፣ የአዳራሽ ውስጥ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ምርጫው ሊካሄድ ሶስት ሳምንት ሲቀር በተመሳሳይ ሰዓት፣ በየፊናቸው ሆነው በተናጥል ያካሄዱት ውይይት በተሌቪዥን የተላለፈው ሲሆን ውይይቱን የተከታተለው፣ የቪኦኤ ዘጋቢ ማይክ ኦስሉቪያን ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል፡፡

መጀመሪያ የታበው ሁለቱ እጩዎች በአካል ተገናኝተው ግንባር ለግንባር ክርክር እንዲያደርጉ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ህዳር ሁለት ቀን ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለኮቪድ -19 መጋለጣቸው በመነገሩ ውይይቱ በአካል መሆን ቀርቶ በርቀት በኢንተርኔት እንዲሆን በአዘጋጆቹ ተወሰነ፡፡ ትራምፕ ግን በአካል ካልሆነ በርቀት ኢንተርኔት ላይ አላደርግም አሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ሁለቱም እጩዎች አፎካካሪ በሆኑት አሻሚዎቹ ክፍለግዛቶች፣ ፐንሴልቬን ያና ፍሎድሪ ላይ የአዳራሽ ውስጥ የጥያቄና መልስ ውይይት አዘጋጁ፡፡ ከህዝብ በተሰበሰበው የአስተያየት ድምጽ መሰረት ትራምፕ በባይደን ተቀድመዋል፡፡ በዚህ የተነሳ በህመም ላይ የነበሩበትንም ጊዜ ለማካካስ እየተሯሯጡ ነው፡፡ በኤንቢሲ ቴሌቪዥን በተላለፈው ዝግጅታቸው ላይ ትራምፕ እንዲህ አሉ፣

“ ዛሬ በኖርዝ ካሮላይና ነበርኩ፡፡ በርካታ ሰው የተገኘበት፣ በጣም ትልቅ ዝጅግት ስለነበር ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶኛል፡፡ ፍሎሪዳም ፔንሰልቬን ያም በሁሉም ቦታ አለን፡፡”

ትረምፕ ኮቪድ 19ን አስመልከቶ እየሰሩ ያሉትን ሥራ በማድነቅ፣ በተለይም ባለፈው ጥር ወር ከቻይና የሚመጡ በረራዎችን ማገዳቸውን አንስተው ጥሩ መስራታቸውን ተናግረዋል፡፡ በኤንቢስ ቴሊቪዥን በተላለፈው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት ተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን ግን ፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለኮቪድ -19 የሰጡት ምላሽ በደረጃው የወደቀ ነው በማለት እንዲህ ብለዋል

“መምራት የፕሬዚዳንት ኃላፊነት ነው፡፡ እሳቸው ግ ን ይህን አላደረጉም፡፡ ምን መደረግ እንዳለበት መናገር ይፈራሉ፡፡ ምክ ያቱም እኔ እንደሚመስለኝ ለስቶክ ማርኬቱ (ለአክስዮን ገበያው) ዝምብለው እየተጨነቁ ነው፡፡”

ባይደን ትራምፕ የክፍለ ግዛቶቹን ገዢዎችና ከንቲባዎቹ የመከላከሉንና መመሪያውን እንዲጠብቁ ጫና ቢያሳድሩባቸው ኖሮ ብዙ ህይወት በዳነ ነበር ብለዋል፡፡ በሌላም በኩል ለጠቅላይ ፍርድ ዳኝነት የታጩት ኤሚ ካኒ ባሬት ጉዳያቸው በዚህ ሳምንት በሴኔት ኮሚቴው እየታየ ሲሆን እጩነታቸው ከጸደቀላቸው አካራካሪ የሚሆን የምርጫ ውጤት ቢኖር በውሳኔው ምንነት ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረው ይገመታል፡፡

“ ይህ ሙሉ ለሙሉ የእሳቸው ምርጫ ነው፡፡ ወይ ለእኔ ወይም በ እኔላይ ሊወስኑ ይችላሉ፡፡ ምንም ይሁን ምን ግን ማዳላት እሚኖርበት ምክንያት አይታየኝም፡፡”

ባይደን የጠቅላ ፍርድቤቱን ሚዛን ለመጠበቅ የዳኞች ቁጥር እንደማይጨምሩ ቃል መግባቱን አልፈለጉም፡፡ እንዲህ ብለዋል

“ለነገሩ እኔ የዚህ ነገር ደጋፊ አይደለሁም፡፡ ለማንኛውም ግን ወደፊት እንድምናየት ውጤት የሚወሰን ይሆናል፡፡”

እጩዎቹ በአንድ ነገር ተስማምተዋል

“ምርጫ እየመጣ ነው፡፡ ይህ በአገራችን ታሪክ እጅግ በጣም ወሳኙ ምርጫ ይመስለኛል፡፡”

ባይደን ከተመረጡ ከሪፐብሊካን ጋር አብረው ለመስራት ቃል ገብተዋል፡፡

“ምክንያቱም ልንግባባ የምንችልባቸው በጣም ብዙ ጉዳዮች አሉን፡፡”

ፓርቲዎቹን የሚለያይዋቸው በርካታ ነገሮች ግን አሉ፡፡ በብዙ ክፍል ግዛቶች ድምጽ መሰጠቱ ቀደም ብሎ የተጀመረ ሲሆን ትራምፕ ግን መጠነ ሰፊ የሆነ ማጭበርበር ሊኖር እንደሚችል እያስጠነቀቁ ነው፡፡ ብዙዎቹ የምርጫ ባለሙያዎች ግ ን ይህ ዓይነቱ ነገር ተፈጥሮ አለማወቁን ይናገራሉ፡፡ ፕሬዚዳንት አንድ ጥያቄ ቀረበላቸው፡፡ እርስዎ በምርጫው ቢሸነፉ ውጤቱን ይቀበላሉ? የሚል፡፡ እንዲህ ብለው መለሱ

“መልሱ እቀበላለሁ ነው፡፡ ግን የሚታመን ምርጫ እንዲሆን እፈልጋለሁ፡፡ ሌላውም ሰው ሁሉ የሚፈልገው ይህንኑ ነው፡፡”

እጩዎቹ ካሁን በኋላ ለሚያደርጉት ክርክር ለመጨረሻ ጊዜ አንዴ እንደሚገናኙ ቀደም ሲል የተያዘው የጊዜ ሰሌዳ፣ ያመለክታል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ትራምፕና ባይደን ከመራጮች ጋር ለጥያቄና መልስ ተገናኙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:26 0:00


XS
SM
MD
LG