በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ አስተዳደር የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር ሠራተኞችን ማባረር ጀምሯል 


የአሜሪካ አየር መንገድ ንብረት የኾነው የመንገደኞች አውሮፕላን ከወታደራዊ ሄኪኮፕተሩ ከተጋጨ በኋላ አንድ ሰው ሬገን ብሄራዊ አውሮፕላን ማረፊያ የቁጥጥር ማማ ላይ በመሆን በምልክት እየገለፀ፤ ዋሺንግተን ዲሲ እአአ ጥር 30/2025
የአሜሪካ አየር መንገድ ንብረት የኾነው የመንገደኞች አውሮፕላን ከወታደራዊ ሄኪኮፕተሩ ከተጋጨ በኋላ አንድ ሰው ሬገን ብሄራዊ አውሮፕላን ማረፊያ የቁጥጥር ማማ ላይ በመሆን በምልክት እየገለፀ፤ ዋሺንግተን ዲሲ እአአ ጥር 30/2025

የትራንስፖርት ሚንስቴር "ወሳኝ የበረራ ደኅንነት ሠራተኞች አልተባረሩም" ብሏል

ሠራተኞቹን የማስወጣቱ ርምጃ የተጀመረው ቁጥሩ የበዛ ሰው በአውሮፕላን በሚጓጓዝበት ያለፈው ሳምንት መጨረሻ ከመኾኑም ሌላ ባለፈው ጥር ወር በሬገን ዋሽንግተን አውሮፕላን ጣቢያ ሁለት አውሮፕላኖች አየር ላይ ተጋጭተው የበርካታ ሰዎች ህይወት ከጠፋበት አደጋ በሳምንታት ተከትሎ ነው።

የአቪየሽን ደኅንነት ባለሞያዎች ማኅበር ፕሬዝደንት ዴቪድ ስፔሮ ባወጡት መግለጫ ወደ ቋሚ ሠራተኝነት መሸጋገሪያ ክትትል ወቅት ላይ ያሉ የቅርብ ጊዜ ተቀጣሪዎች "ከሥራ ተሰናብታችኋል" የሚለው የኢሜል ደብዳቤ የደረሳቸው ባለፈው ዓርብ ማታ መሆኑን አመልክተዋል።

ማንነቱ እንዳይገለጽ የጠየቀ የበረራ ትራፊክ ተቆጣጣሪ ለአሶሲየትድ ፕሬስ በሰጠው ቃል ከተባረሩት መካከል የራዳር ክትትል ባለሞያዎች እና አብራሪዎችን አውሮፕላን በማሳረፍ እና በበረራ ሂደት የሚረዱ ባለሞያዎች ጭምር እንዳሉባቸው ተናግሯል።

የትራንስፖርት ሚንስቴር በበኩሉ ትላንት ሰኞ ማታ ለአሶሲየትድ ፕሬስ በሰጠው ቃል "በሠራተኛ ቅነሳው አንድም የአየር ትራፊክክ ተቆጣጣሪ አልተነካም። መሥሪያ ቤቱ ወሳኝ የሆኑ የበረራ ደኅንነት ሥራ ላይ ያሉ ሠራተኞች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ አድርጓል" ብሏል።

በማስከተልም "የሚያርፉ አውሮፕላኖች የሚከታተሉ እንዲሁም የበረራ እቅድ ርዳታ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች ሥራ ወሳኝ የደኅንነት ሥራ ተብሎ ሊመደብ ይችል እንደሆነ ማጤን ይኖርብናል" ማለቱንም አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

የበረራ ትራፊክ ቁጥጥር ሠራተኞች ማኅበር ትላንት ሰኞ ባወጣው አጭር መግለጫ የተባለው የሠራተኞቹ መባረር በሀገሪቱ የአየር ክልል ደኅንነት ሥርዐት እንዲሁም በማኅበሩ አባላት ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት በመገምገም ላይ እንደኾነ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG