በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምክር ቤቱን በመድፈር 4 ወራት በእስራት ያሳለፉት የትረምፕ አጋር ስቲቭ ባነን ተፈቱ


የዶናልድ ትረምፕ የረዥም ጊዜ አጋር የሆኑት ስቲቭ ባነን
የዶናልድ ትረምፕ የረዥም ጊዜ አጋር የሆኑት ስቲቭ ባነን

የዶናልድ ትረምፕ የረዥም ጊዜ አጋር የሆኑት ስቲቭ ባነን ምክር ቤቱን በመድፈር 4 ወራት በእስራት ካሳለፉ በኋላ ዛሬ ማክሰኞ ተፈተዋል፡፡

ባነን ለእስር ያበቃቸው እኤአ ጥር 6፣ 2021 በምክር ቤቱ ህንጻ ላይ ስለተፈጸመው ጥቃት ለተደረገው ምርመራ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ የቀረበውን ትእዛዝ ለመቀበል እና ትረምፕ እኤአ የ2020 የምርጫውን ውጤት ላለመቀበል ፈጽመውታል ከተባለው ክስ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ለማቅረብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው፡፡

ባነን በነገው ቀን በማንሃተን ኒው ዮርክ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት አቅደው እንደነበር ተወካያቻው ተናግረዋል።

በኢንተርኔት የሚያስተላልፉት (የፖድካስት) ስርጭታቸው ዛሬ ማክሰኞ ጀምሮ ይቀጥላል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ባነን በዩናይትድ ስቴትስ እና በሜክሲኮ ድንበር ግንብ እንዲገነባ ገንዘብ የሰጡ ለጋሾችን በማጭበርበር በኒውዮርክ ግዛት ፍርድ ቤት ተጨማሪ የወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።

በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በማሴር፣ በማጭበርበር እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች የተከሰሱት ባነን “ጥፋተኛ አይደለሁም” ብለዋል።

በዚህ ጉዳይ የፍርድ ሂደት በታህሳስ ወር ሊጀመር ቀጠሮ ተይዟል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG