በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ አሜሪካ ከቻይና ጋር የንግድ ጦርነት እያካሄደች አይደለም አሉ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ረቡዕ አሜሪካ ከቻይና ጋር የንግድ ጦርነት እያካሄደች አይደለም ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ረቡዕ አሜሪካ ከቻይና ጋር የንግድ ጦርነት እያካሄደች አይደለም ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ቻይና በዩናይትድ ስቴትስ ዕቃዎች ላይ የ$50 ቢልዮን ዶላር ቀረጥ እንደምትደነግግ ካስታወቀች በኋላ ነው። አሜሪካ ለወሰደችው ተመሳሳይ እርምጃ ምላሽ መሆኑ ነው።

ትረምፕ ትላንት በትዊተር ባስተላለፉት መልዕክት “ከቻይና ጋር የንግድ ጦርነት እያካሄደን አይደለም፣ እንዲህ ዓይነቱ ጦርነት ዩናይትድ ስቴትስን በወከሉ ብቃት በጎደላቸው ዋጋ ቢስ ሰዎች ጠፍቷል” ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በየዓመቱ የ $500 ቢልዮን ዶላር የንግድ ኪሳራ ይደርስብናል። በአዕምሮ ንብረት ስርቆት ደግሞ ሌላ $300 ቢልዮን ዶላር እያጣን ነው” በማለትም ፕሬዚዳንቱ አክለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG