በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሥልጣን ከተረከቡ 500 ቀናቸውን ደፍነዋል

የዩናይትድ ስቴስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሥልጣኑን ከተረከቡ ዛሬ 500 ቀናቸውን ደፍነዋል። ከማንኛውም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የበለጠ ብዙ ሥራ ማከናወኔን “ብዙ ሰዎች ያምናሉ” ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሥልጣኑን ከተረከቡ ዛሬ 500 ቀናቸውን ደፍነዋል። ከማንኛውም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የበለጠ ብዙ ሥራ ማከናወኔን “ብዙ ሰዎች ያምናሉ” ብለዋል።

የግብር መጠን መቀነሱን፣ በሃገሪቱ ወታደራዊ ኃይል መዳበርን፣ ወንጀልና ህግ-ወጥ ፍልሰት መቀነስን፣ የድንበር ጥበቃ መጠከርንና የኢኮኖሚ እድገትን ካስገኝዋቸው ስኬቶች መካከል ናቸው ብለዋል።

የትረምፕ ፕሬዚዳንትነት 17ኛ ወሩን በያዘበት በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱን የከፋፈሉ ሰው ተደርገው መታየታቸው ቀጥሏል። የህዝብ መለክያ አሀዞች እንደሚያሳዩት በሥራቸው ከሚረኩት የማይረኩት ያይላሉ። ያልረኩት 52.8 ከመቶ ሲሆኑ የረኩት 44.4 ናቸው። ከሩስያ የምርጫ ጣልቃ-ገብነት ጋር ግንኙነት ይኖራቸው እንድሆነ ለማጣራትም ለአንድ ዓመት ያህል ምርመራ እየትካሄደባቸው ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG