በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አምስት ቀን ቀረው


ፎቶ ፋይል፦ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና የቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ደጋፊዎች ፍሎሪዳ
ፎቶ ፋይል፦ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና የቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ደጋፊዎች ፍሎሪዳ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከአምስት ቀን በኋላ የፊታችን ማክሰኞ እአአ ህዳር ሦስት ቀን ያካሄዳል። ተፎካካሪዎቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና የቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የዛሬውን የምረጡን ቅስቀሳቸውን ደቡብ ምስራቋ ፍሎሪዳ ክፍለ ግዛት ላይ አነጣጥረው ይጀምራሉ።

እኤአ ከ1996 ወዲህ ለአሸናፊነት የበቁ ዕጩዎች በሙሉ ፍሎሪዳን ያሸነፉ እንደሆኑ ይታውሳል።

ለመመረጥ የሚያበቃውን 270ውን የክፍለ ግዛቶች ወይም የስቴቶች መራጭ ተወካዮች ድምፅ ውስጥ ፍሎሪዳ ሃያ ዘጠኝ ድምጽ አላት።

ትረምፕ የምረጡን ቅስቀሳቸውን ታምፓ ላይ ጀምረው ማታ ደግሞ ወድሰሜን ካሮላይና ይጉዋዛሉ። ባይደን ደግሞ ዛሬ ከቀትር በኋላ ፍሎሪዳዋ ብራዋርድ አውራጃ ላይ ይቀሰቅሱና ለማታው ወደ ታምፓ ይሄዳሉ።

XS
SM
MD
LG