በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ አሟሟት የድምፅ ቅጂ መረጃ

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ
የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ

ባለፈው ወር ቱርክ ኢስታንቡል በሚገኘው የሳዑዲ ዓረብያ ቆንስላ የተገደለውን ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ አሟሟት የሚመለከተውን የድምፅ ቅጂ ሃገራቸው ማዳመጧን የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ተናገሩ።

ባለፈው ወር ቱርክ ኢስታንቡል በሚገኘው የሳዑዲ ዓረብያ ቆንስላ የተገደለውን ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ አሟሟት የሚመለከተውን የድምፅ ቅጂ ሃገራቸው ማዳመጧን የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ተናገሩ።
ቱርክ መረጃዎችዋን በሙሉ ለካናዳ አጋርታለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ አስታውቀዋል።

ቅዳሜ ዕለት የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይፕ ኤርዶዋን በሰጡት ቃል እጃችን ያለውን የድምፅ ቅጂ ለእንግሊዝ ለፈረንሳይ ለጀርመን ለሳዑዲ ዓረብያና ለዩናይትድ ስቴትስ ሰጥተናል ማለታቸው ይታወሳል።
ዣማል ኻሾግዢ እ ኤ አ ጥቅምት ሁለት ቀን ኢስታንቡል የሚገኘው የሳዑዲ ዓረብያ ቆንስላ ለጉዳይ ገብተው በዚያው ደብዛቸው መጥፋቱ ይታወሳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG