በአማራ ክልል፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ከጎንደር ወደ ባሕር ዳር መስመር ወደ ውጭ የሚላክ ሰሊጥ ጭነው በመጓዝ ላይ በነበሩበት ወቅት "ጣራ ገዳም " በተባለ ቦታ፣ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው፣ አንድ አሽከርካሪ መገደሉን፣ አንድ መቁሰሉን እና ሌሎች ዐሥር አሽከርካሪዎች መታገታቸውን፣ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁና ለደኅንነታቸው ስለሚሰጉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ ተናገሩ።
የአማራ ክልል መንግሥት፣ ለክልሉ ብዙኅን መገናኛ በሰጠው መግለጫ፣ “ጽንፈኛ” ሲል የጠራው ታጣቂ ቡድን አድርሶታል ባለው ጥቃት፣ ስድስት ሰሊጥ የጫኑ ከባድ መኪኖችን መቃጠላቸውን አስታውቋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም