በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመንግስት ብድር ለህንጻ ተቋራጮች የተገዙ የገልባጭ መኪናዎች ታገዱ


እነዚህ የጭነት መኪናዎች በ70 ከመቶ የመንግስት ብድር ተገዝተው ከቀረጥ ነጻ ለግል የግንባታ ኩባንያዎች የተሰጡ ናቸው
እነዚህ የጭነት መኪናዎች በ70 ከመቶ የመንግስት ብድር ተገዝተው ከቀረጥ ነጻ ለግል የግንባታ ኩባንያዎች የተሰጡ ናቸው

የኢትዮዽያ መንግስት የቤቶችና የከተማ ልማት ሚንስትር የግል የግንባታ ኩባንያዎችን ለማጠናከር በሚል 70 ከመቶ ብድር በመስጠት ገልባጭ መኪኖችን ከቀረጥ ነፃ እንድያስገቡ ፈቅዷል።

ይህም የተደረገው ኩባንያዎቹ የመንግስት የጋራ ቤቶችን (ኮንዶሚኒየም) እንዲሰሩ በሚል እንደሆነም ተገልጿል።

በዚህ መሃል መንግስት የጋራ ቤቶች ግንባታ ከአዲስ አበባ በስተቀር በሌሎች ክልሎች በመገንባት ላይ ያሉት ህንጻዎች እስኪጠናቀቁ ደረስ እንዲቆም በማድረጉ የግል ኩባንያዎቹ ወደ ሌላ የግንባታ ስራ ተሰማሩ።

የግል ኩባንያዎቹ ከመንግስት የንግድ ባንክና ከክልሎች የቤቶች ግንባታ ኤጄንሲዎች ጋር በገብቡት ውል ላይ መንግስት የጋራ ቤት ግንባታ ስራ ባይጣቸው በሌሎች የግንባታ ስራዎች ተሰማርተው ብድራቸውን መመለስ እንደሚገባችውም ፈቅዷል።

በዚህ መሰረት ኩባንያዎቹ መኪኖቹን አከራይተው ሲሰሩባቸው ጉምሩክ በደረሰው ጥቆማ መሰረት መኪኖቹን እየያዘ ማሸግ ጀምሯል። ባንክም የሓርጅ ማስታወቂያ አውጥቷል።

በዚሁ ምክንያት ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ 32 የህንጻ ተቁዋርጭ ድርጅቶች ይህንን የመንግስት እርምጃ በመቃወም አቤቱታ በማሰማት ላይ ናቸው።

መቀሌየሚገኘው የሰሜን ኢትዮዽያ የጉምሩክ እና የገቢዎች ባለስልጣን ጽህፈት ቤት ስራ አስከያጅ አቶ ሙሉጌታ ሮቤል ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት መግለጫ መንግስትና የግል ኩባንያዎች የገቡት ውል ከሃገሪቱ የጉምሩክ ህግ ጋር ይቃረናል ብለዋል።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG