ድሬዳዋ፣ ሀዋሳ —
በሶማሌ ክልል አስራ አንዱ ዞኖችና ስድስቱ የከተማ አስተዳደሮች ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሂዷል። ህወሓት ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በተለየ በሶማሌ ላይ የከፋ ግፍ ፈጽሟል ያሉት የክልሉ አመራሮች አሁን የህወሓት አመራሮችን ለህግ ለማቅረብ የተጀመረውን ዘመቻ እንደግፋለን ብለዋል።
በምስራቅ ሃረርጌ ሦስት ወረዳዎች ተመሳሳይ ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን ከ150 በላይ ሰንጋዎች ለመከላከያ ሰራዊቱ ተበርክተዋል።
በሌላም በኩል ህወሓት በሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማ፣ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥትና በኦሮምያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ተደርጓል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡