በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጀርመኑ የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው


 ፎቶ ፋይል፡ የተጠረጠሩት ሃይንሪሽ 13ተኛ ልዑል ሩስ’ን በፖሊስ ሲወሰዱ ፍራንክፈርት፤ ጀርመን እአአ 2022
ፎቶ ፋይል፡ የተጠረጠሩት ሃይንሪሽ 13ተኛ ልዑል ሩስ’ን በፖሊስ ሲወሰዱ ፍራንክፈርት፤ ጀርመን እአአ 2022

ራሳቸውን ልዑል አድርገው የሰየሙትን የጀርመኑ የቀኝ ዘመም የፖለቲካ ፓርቲ የቀድሞ የምክር ቤት አባል ጨምሮ፣ የሃገሪቱን መንግሥት ለመገልበጥ ከተወጠኑ ሦስት ድርጊቶች ጋራ በተያያዘ የተወነጀሉ ዘጠኝ ዋና ዋና ተጠርጣሪዎች በመጭው ወር ጉዳያቸው መታየት እንደሚጀምር ይፋ ተደርጓል።

የፍራንክፈርቱ የፌደራል ችሎት፣ በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2022 ዓ.ም. መገባደጃ የተደረሰበት የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ ዋና ዋና ተጠርጣሪዎች ጉዳይ የፊታችን ግንቦት 13 መታየት ይጀምራል። የክስ ሂደቱ እስከመጭው የአውሮፓውያኑ 2025 ድረስ ይዘልቃል ብሎ እንደሚጠበቅም ፍርድ ቤቱ ጨምሮ አመልክቷል።

የፌደራሉ አቃብያነ ሕግ ባለፈው ታኅሳስ ወር ነበር፣ አሁን በሕይወት የሌሉ አንድ ተከሳሽን ጨምሮ በአጠቃላይ በወንጀሉ በተጠረጠሩ 27 ሰዎች ላይ የሽብርተኝነት ክስ የመሰረቱት። የፍራንክፈርቱ የክስ መዝገብ ቡድኑ ቀጣዩ የጀርመን የሽግግር ወቅት መሪ አድርገ ሊሾመው ያቀደውን ሃይንሪሽ 13ተኛ ልዑል ሩስ’ን፣ ሌላውን የጀርመን የቀኝ ዘመም የፖለቲካ ፓርቲ የቀድሞ የምክር ቤት አባል እና ዳኛ ብርጂት ማልሳክ-ዊንክማን’ን እንዲሁም ጡረተኛውን የቀድሞ ልዩ ጦር አባልን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ግለሰቦችን እንዳካተተ ይታወቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG