ዋሺንግተን ዲሲ —
ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት የሚከለክለው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጉዞ እገዳ፣ በሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መሻሩ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት እገዳው ተግባራዊ ሳይሆን ቢቆይም፣ የሕገ መንግሥታዊነቱ ጉዳይ ግን እየታሰበበት ነው።
የትራምፕ አስተዳደር ይግባኝ እንደሚል ገልጧል።
የሆነ ሆኖ፣ እገዳው ሥራ ላይ ሳይውል ቢቆይም፣ ተቃዋሚ ወገኖች ግን ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ከማድረግ አልታቃቡም።
“ሙስሊሞች ከእንግዲህ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አይገቡም” የሚለውን የፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እገዳ የሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፈኞች ዋይት ሀውስ ቤተ መንግሥት ፊት ለፊት ተሰባስበዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ