በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካርቱም ከወላጅ አልባ ህጻናት ማሳደጊያ መውጫ ያጡ በርካታ ህጻናት ሞቱ


አስቸኳይ ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ህጻናት ዩኒሴፍ እርዳታ አድርሷል፡፡
አስቸኳይ ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ህጻናት ዩኒሴፍ እርዳታ አድርሷል፡፡

ውጊያ በሚካሄድባት የሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ከነበሩበት ወላጅ አልባ ህጻናት ማሳደጊያ መውጫ አጥተው በአሰቃቂ ሁኔታ ከከረሙ ብዙ ህጻናት መካከል ቢያንስ 60 ጨቅላ እና ህጻናት መሞታቸው ተነገረ፡፡አብዛኞቹ ህጻናት የሞቱት በረሃብ እና በትኩሳት ምክንያት ሲሆን ሀያ ስድስቱ የሞቱት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሁለት ቀን ውስጥ መኾኑ ተዘግቧል፡፡

አል ማይኮማ በተባለው የወላጅ አልባ ህጻናት ማሳደጊያ በህጻናቱ ላይ የደረሰውን ከባድ ስቃይ አሶሺየትድ ፕሬስ ያነጋገራቸው በርካታ ሐኪሞች፣ በጎ ፈቃደኛ ሠራተኞች ፣ የጤና ባለሥልጣናት እና ሠራተኞች ገልጸዋል፡፡ ህጻናቱ የከረሙበትን አሰቃቂ ሁኔታ የሚያመለክቱ ሰነዶች፣ ምስሎችና የቪዲዮ መረጃዎች ማየቱን ገልጿል፡፡

በግጭቱ የደረሰውን ጉዳት የሚከታተለው የሱዳን ዶክተሮች ቡድን፣ እኤአ ከሚያዝያ 15 ወዲህ፣ ቢያንስ 190 ህጻናትን ጨምሮ 860 ሰላማዊ ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን አመልክቷል፡፡ የደረሰው ጉዳት ከዚህም በላይ እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት አስቸኳይ ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ህጻናት ቁጥር 9 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን አሁን 13.6 ሚሊዮን መድረሱን ዩኒሴፍ አስታውቋል፡፡ አሶሽየትድ ፕሬስ ያገኘው ሰነድ እንደሚያሳየው እስካለፈው ሰኞ ድረስ በህጻናት ማሳደጊያ ቢያንስ 341 ህጻናት ነበሩ፡፡ 165ቱ ከአንድ እስከ ስድስት ወር ዕድሜ ውስጥ ያሉ መኾናቸው ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG