ዓለም አቀፉ የጸረ ሙስና ድርጅት ‘ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል’ በያዝነው ሳምንት ይፋ ባደረገው የሀገራት የሙስና ይዞታ ዓመታዊ ሪፖርቱ እንዳመለከተው፡ 72 ነጥብ ያስመዘገበችው ሲሼልስ ከአፍሪካ ሀገራት በሙሉ በሙስና ዝቅተኝነት ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን፤ ካቦ ቨርዲ በ62፣ ቦትስዋና በ57፣ ሩዋንዳ ደግሞ በ57 ነጥቦች በደረጃው ሰንጠረዥ ተከታታዩን እርከኖች ተቆናጠዋል።
በሪፖርቱ መሰረት ክፉኛ በሙስና የተዘፈቁት የአፍሪካ ሀገራት ተርታ 8 ነጥብ ያስመዘገበችው ሶማሊያ 9 ነጥብ ያስመዘገበችው ደቡብ ሱዳን፡ እንዲሁም በተመሳሳይ 13 ነጥቦች ያስመዘገቡት ሊቢያ፣ ኤርትራ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ይገኙባቸዋል። ከሁለት ዓመት በፊት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2023 ከወጣው መረጃ ጋራ ሲነጻጸር ኤርትራ በ8 ነጥብ ዝቅ በማለት ከቀድሞውም በከፋ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
በ99ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ ዘንድሮም እንዳለፈው ዓመት 37 ነጥብ ነው ያስመዘገበችው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ዴንማርክ በ90 ነጥብ በሙስና ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ፊንላንድ በ88 ነጥብ፣ ሲንጋፖር ደግሞ በ84 በሁለተኛ እና በሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ዩናይትድ ስቴትስ በአንጻሩ በ65 ነጥብ 28 ላይ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
መድረክ / ፎረም