በሲዳማ ክልል ምስራቅ ሲዳማ ዞን ቦና ዙሪያ ወረዳ፣ የተከሰተውና የ71 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የመኪና አደጋ ምክኒያት በገላና ወንዝ ላይ ድልድይ የተሠራበት ከፍተኛ መታጠፊያና ቁልቁለት መኾኑን የዐይን እማኞች እና ትራፊክ ፖሊስ ተናገሩ።
አካባቢው ተደጋጋሚ አሰቃቂ የመኪና አደጋዎች እንደሚከሰትበት የአከባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የክልሉ እና ፌዴራል መንግሥታት የመፍትሔ ርምጃ እንዲወስዱ አቤቱታ አቅርበዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም