የትራምፕ አስተዳደር ለደቡብ ሱዳን ዜጎች በጊዚያዊ መልክ በዩናይትድ ስቴትስ የመቆየት ፈቃዳቸው እንዲራዘም ወስኗል። ለሱዳን ተወላጆች የሚሰጠው ፈቃድ ግን በመጪው አመት ያበቃል።
የዩናይትድ ስቴትስ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር በሱዳን ያለው ሁኔታ በመጠኑ ስለተሻሻለ ለዛች ሀገር ዜጎች ጊዚያዊ መጠለያ መስጠት አስፈላጊ አይደለም ሲል ትላንት አስታውቋል። የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በሰላም ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ለማይችሉት ወይም ሀገራቸው ልትረዳቸው ለማትችለው ዜጎች በጊዚያዊ መልክ የመኖርያ ፈቃድ እንዲያገኙ ያደርጋል።
ለሱዳናውያን የሚሰጠው ማኖርያ ፈቃድ እአአ በመጪው ህዳር 2 ቀን ወር ሊያበቃ ነበር። ይሁንና ለአንድ ዓመት ብቻ ተራዝሟል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ