በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"አቶ ጌታቸው ረዳ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ናቸው" - አቶ አማኑኤል አሰፋ


በቅርቡ በተካሄደው አወዛጋቢ የህወሓት ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ
በቅርቡ በተካሄደው አወዛጋቢ የህወሓት ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ
"አቶ ጌታቸው ረዳ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ናቸው" - አቶ አማኑኤል አሰፋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:16 0:00

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው ቡድን ባካሄደው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመኾናቸው ፕሬዝደንትነታቸውን እንደማይቀበል፣ በቅርቡ በተካሄደው አወዛጋቢ የህወሓት ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ኾነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ ተናገሩ።

አቶ አማኑኤል ዛሬ መቐሌ ላይ በሰጡት መግለጫ አቶ ጌታቸውን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሲሉ ጠርተዋቸዋል። "የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት እና ወደ ኅበረተሰቡ የማቀላቀል ሥራ፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እየተሠራ አይደለም" ያሉት አቶ አማኑኤል ሂደቱን ተቃውመውታል።

አቶ አማኑኤል ዛሬ ረቡዕ ኅዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ለብዙኀን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ህወሓትን በአመፅ ለመበተን ወጣቶች እያሰለጠኑ ናቸው ሲሉ ወንጅለዋል።

በጉዳዩ ላይ ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ሆኖም የአስተዳደሩ ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ በቅርቡ፣ በሰጡት መግለጫ፣ በዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራ የህወሓት ቡድን፣ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ሥራውን እንዳያከናውን ከማድረግ በተጨማሪ የወረዳ ምክር ቤቶች በመጠቀም በመንግሥት የተመደቡ አስተዳዳሪዎች እንዲነሱ እያደረገ ነው ፣ "ይህ መፈንቅለ መንግሥት” ነው " ሲሉ ከሰው ነበር።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG