መቀሌ —
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት “ኦነግ ሸኔ” ከሚሉትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ከፈረጀው፤ ራሱን “የኦሮሞ ነፃነት ጦር” ብሎ ከሚጠራው የታጠቀ ቡድን ጋር ለመሥራት ስምምነት የደረሰው “ሃገርን እና ህዝብን ወደ ገደል እየከተተ ያለ የጥፋት ኃይል” ያለውን በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የሚመራውን የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ለመዋጋት ነው ሲል የፌዴራሉ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀው እና ክልሉን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት ባወጣው መግለውጫ አስታወቀ።
በአፋር ክልል በንጹሃን ላይ የደረሰውን ፍጅት በገለልተኛ ዓለም አቀፍ ተቋም እንዲጣራ እንደሚፈልግም በመግለጫው አመልክቷል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።