በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ “አንገኝም” ላሉ የፓርቲው አመራሮች የተሳትፎ ጥሪ ተደረገ


መቐለ ከተማ
መቐለ ከተማ
በህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ “አንገኝም” ላሉ የፓርቲው አመራሮች የተሳትፎ ጥሪ ተደረገ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:56 0:00

በመቐለ ከተማ እየተካሔደ ባለው አወዛጋቢው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፉ ይፋ ላደረጉ የፓርቲው አመራሮች፣ በአካል ተገኝተው ሐሳባቸውን እንዲገልጹ ጥሪ መቅረቡን፣ የጉባኤው ቃል አቀባይ አቶ ዐማኑኤል አሰፋ አስታወቁ፡፡

ከትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞንና ከደቡባዊ ምሥራቅ ዞን ሁለት ወረዳዎች የተወከሉ ጉባኤተኞች፣ “በአመራሮች ጫና ሳይሳተፉ ቀርተዋል፤” ብለዋል አቶ ዐማኑኤል፡፡

በጉባኤው ላይ እንደማይሳተፉ ከገለጹ 14 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አንዱ እና የትግራይ ደቡባዊ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቱ ኪሮስ ግን፣ የዞናቸው ተወካዮች በጉባኤው ያልተሳተፉት፣ “ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች በመኖራቸውና ጉባኤውም ሕጋዊ አለመኾኑን በመቃወም እንጂ በአመራር ጫና አይደለም፤” ብለዋል፡፡

በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሦስት ፓርቲዎች በሰጡት መግለጫ ደግሞ፣ “ለሥልጣን የበላይነት ለሁለት ተከፍሎ እየተሻኰተ ነው፤” ያሉት የህወሓት አመራር ውዝግብ ወደ ግጭት እንዳያመራ አስጠንቅቀዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG