ለሁለት ከተከፈሉት የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች፣ በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ዛሬ መቐለ ከተማ ላይ ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋራ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል።
“እምቢ የማለት ዘመቻ” የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚህ ውይይት መክፈቻ ላይ የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ በትግራይ ክልል በአሁኑ ጊዜ ልዩ ትግል እና መደጋገፍ እንደሚያስፈልግ መግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል፣ ሦስት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች በአራት የትግራይ ዞኖች ዳሰሳ ማካሔዳቸውን ገልጸው በሰጡት መግለጫ፣ ህወሓትን ትጥቅ በማስታጠቅ ከሰዋል።
በዶክተር ደብረ ጽዮን የሚመራው የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የኾኑት፣ ዶክተር ፍሰኻ ሀብተ ጽዮን፣ “እኛ ፓርቲ ነን ማስታጠቅም መመልመልም አንችልም፣ ትግላችንም ሰላማዊ ነው” ብለዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም