ዋሺንግተን ዲሲ —
ሕወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ሁለት ወራት ለሚጠጋ ጊዜ ስበሰባና ግምገማ አካሂዶ በሥራ አስፈፃሚ አባላት ላይ የማገድና ከሥልጣናቸው የማንሳት እርምጃ መውሰዱ ይታወሳል። በትላንትናው ዕለት ደግሞ አዲስ ሊቀመንበር መርጦ ሌሎች አዳዲስ ሰዎችን ተክቷል። በዛሬ ዕለት ባወጣው መግለጫም አዲሱ አመራር ለጋራ ፌዴራላዊት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ የተጫወተውን ገንቢ ሚና አጠናክሮ ለመወጣት የሚያስችለውን አቅጣጫዎች ከሕዝቦች ጋር በመመካከር እንደሚያከናውን አስታውቋል፡፡
ይህንን አጠቃላይ የሕወሓት ግምገማና ሹም ሽር በተመለከተ፤በትጥቅ ትግልና በድርጅቱ ውስጥ ጉልሕ ስፍራ የነበራቸው የቀድሞ ታጋይ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የአረና ፓርቲ አባልና የመድረክ ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑትን አቶ ገብሩ አስራትን ጽዮን ግርማ አነጋግራቸዋች።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ