በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የህወሓት ከፍተኛ የአመራር አባላት ተደመሰሱ ሲል መንግሥት አስታወቀ


አቶ ስዩም መስፍን
አቶ ስዩም መስፍን

የሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ከፍተኛ የአመራር አባላት የነበሩትን “ስዩም መስፍንንና አባይ ፀሐዬን ጨምሮ አራት ሰዎች ተገድለዋል” ሲሉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስቴር የኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብሪጋዲየር ጄነራል ተስፋዬ አያሌው ማምሻውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ስዩም መስፍን ውጊያውን መምራታቸውን ሠራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ማዘዛቸውን በመጨረሻም በሠራዊቱ ላይ ውጊያ አንዲከፈት ማዘዛቸውን ጄነራሉ ተናገረዋል።

ከጠባቂዎቻቸውና ከወታደራዊ ጥበቃ አዛዦቻቸው ጋር ተደመሰሱ ከተባለው ውስጥ የህወሓት ከፍተኛ መሪዎች የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደሣላሴና ኮ/ል ኪሮስ ሃጎስ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

ሌሎች አራት የቀድሞ ወታደራዊ አዛዦችና አንድ ሲቪል መያዛቸውንም ጄነራል ተስፋዬ አያሌው አመልክተዋል።

(ከብሪጋዲየር ጄነራል ተስፋዬ አያሌው ጋር የተደረገው ቃለ ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የህወሓት ከፍተኛ የአመራር አባላት ተደመሰሱ ሲል መንግሥት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:25 0:00


XS
SM
MD
LG