በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህወሓት ከኤርትራ መንግሥት ጋራ ንግግር ማካሄዱን ገለፀ


የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል
ህወሓት ከኤርትራ መንግሥት ጋራ ንግግር ማካሄዱን ገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:48 0:00

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ ፓርቲያቸው ከኤርትራ አመራሮች ጋራ ከስድስት ወራት በፊት ዱባይ ላይ ውይይት ማድረጉን፣ ሊቀመንበሩ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ።

በዚያ ውይይት ላይ ህወሓትን በመወከል የተሳተፉት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ መሆናቸውን የጠቀሱት ሊቀመንበሩ፣ ውይይቱ የተካሄደው "በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዕውቅና" ነው ብለዋል። ሊቀመንበሩ ዛሬ ጥዋት በመቀሌ ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከኤርትራ መሪዎች ጋር ሌሎች ቀጣይ ግንኙነቶች እንደነበሩም አስረድተዋል። የህወሓቱ መሪ ከኤርትራ አመራሮች ጋር ተደረገ ያሉትን ውይይት አስመልክቶ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ከኤርትራ መንግሥትም ሆነ ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እስካሁን የተሰጠ አስተያየት የለም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG