በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ህወሓት ትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል" - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ህወሓት ትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል፤ ሰሜን እዝን ለመዝረፍም ሙከራ አድርጓል ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ህወሓት የትግራይን ህዝብ ሲጠብቅ የኖረውን ሰራዊት እንደ ባዕድና የወራሪ ኃይል ቆጥሮታል በዴልሻህ በኩልም ጦርነት ከፍቷል ብለዋል።

የመከላከያ ሰራዊት በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሃገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ቀይ መስመር ታልፏል፣ ሃገርንና ህዝብን ለማዳን የመጨረሻ አማራጭ ሆኗል ነው ያሉት፥ አያይዘውም ህዝቡ በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል በየአካባቢው ሊከሰቱ የሚችሉ ትንኮሳዎችን በንቃት እንዲከታተል አሳስበዋል።

መንግሥት የትግራይ ህዝብ እንዳይጎዳ በማሰብ ጦርነት እንዳይከሰት እስከትዕግስቱ ጫፍ ታግሶታ። ጦርነት የሚቀረው ግን በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም ብለዋል።

XS
SM
MD
LG